
ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መውለጃ ወራቸው የደረሰ ነፍሰ ጡርና ጡት የሚያጠቡ ሴት ተፈታኞች በሚቀጥለው ዓመት ተዘጋጅተው እንደ መደበኛ ተፈታኝ መፈተን እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ይሁን እንጂ ፈተናውን ለመፈተን ዝግጁ ከሆነ ጡት የሚያጠቡት ተፈታኞች አንድ ሴት ሞግዚት ይዘው በመግባት እንዲፈተኑ ተገቢው ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን ገልጿል።
የተፈታኞች መብትና ግዴታ እንዲሁም የተከለከሉ ነገሮች በተፈታኟና በሞግዚቷ ላይ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!