የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲሳካ አስተዋጽዖ ላደረገው የአፍሪካ ሕብረት ዕውቅና ተሰጠ።

61

ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደህንነት ኮሚሽን እንዲሁም ቡድን የእውቅና መርሐ-ግብር አካሄደ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቅርቡ አፍሪካ ህብረት ላደረገው አስተዋጽኦ በአጠቃላይና ኢትዮጵያ የሰጠችውን እውቅና አስታውሰዋል፡፡

በአፍሪካ ሕብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት እና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ስኬት ለፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላምና ደህንነት አመራር እና ቡድኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል።

በስምምነቱ ወቅት የተደረሰው ስምምነት አፈጻጻም ቀጣይነት ያለው እድገት እያስመዘገበ መሆኑንና ለተሟላና ወቅታዊ ትግበራም መንግስት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

በአፍሪካ ሕብረት ድጋፍና አስተዋጽኦ ቀሪ ስራዎች ተግባራዊ እንደሚሆኑም ነው ያመለከቱት።

የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላምና ፀጥታ ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ በበኩላቸው ለፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ስኬት እውቅና በማግኘታቸው አመስግነዋል።

በአንዳንድ የአፍሪካ አገራት ያሉ ግጭቶች ከኢትዮጵያ ልምድ በመውሰድ ወደ መፍትሔ መምጣት እንደሚቻል መማር እንደሚገባ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኢትዮጵያ 200 የሚጠጉ ወረዳዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተባለ።
Next articleግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴን የሚዘክር ሀውልት በአዲስ አበባ አማካይ ቦታ ላይ እንዲገነባ ተጠየቀ።