አርሲ ዩኒቨርሲቲ ለአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የክብር ዶክትሬት ሰጠ።

82

ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ቀነኒሳ በቀለ በኦሎምፒክ፤ በአለም ሻንፒዮና፤ በሀገር አቋራጭ እንዲሁም በአፍሪካ ሻንፒዮና በጠቅላላ ውድ ሀገሩን ብቻ በወከለበት ውድድር ላይ 35 ጊዜ ውድ ሀገሩን ወክሎ እንደተሰለፈ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
35 ጊዜ ሀገር ወክሎ በመሳተፍ የኢትዮጵያ ባለ ሪከርድ ነው።

35 ጊዜ ሀገር ወክሎ 24 ወርቅ ለሀገሩ አምጥቷል – ይህም ሪከርድ ነው።

ከቀነኒሳ ለሀገር በመሰለፍ 24 ወርቅ ሜዳሊያ አምጥቷል።

ቀነኒሳ ከ1999 እስከ 2021 ደረስ 20 አመት የሮጠ ሲሆን ከ1999 አስከ 2014 ለ14 አመት በእያንዳንዱ አመት ያላማቋረጥ በሙሉ ጤና ሮጧል።

በ2015 በጤና ምክንያት ለ2 አመት ያሮጠ ሲሆን በ2019 አንድ ሩጫ ብቻ ሮጧል። በ2020 አንድ ግማሽ ማራቶን ብቻ የሮጠ ሲሆን በ2021 አመትም እስከአሁን አሮጠም።

በ16 አመት የሩጫ ዘመኑ 35 ጊዜ ሀገሩን ወክሏል በአማካኝ በአመት ውስጥ ሁለት ጊዜ ሀገሩን ወክሏል ማለት ነው።

ቀነኒሳ በቀለ በ16 አመት የሩጫ ዘመኑ 170 ኢንተርናሽናል ውድድሮችን አድርጓል።

➙ 5000 ሜትርን 56 ጊዜ ሮጧል።

➙ 3000 ሜትርን 37 ጊዜ ሮጧል።

➙ ሀገር አቋራጭ 21 ጊዜ በተለያየ ርቀት

➙ 10000 ሜትርን 19 ጊዜ ሮጧል።

➙ ማራትን 10 ጊዜ ሮጧል።

➙ 10 ኪ ሜ ጎዳና 6 ጊዜ ሮጧል።

➙ 2000 ሜትር 5 ጊዜ ሮጧል።

➙ 1500 ሜትር 4 ጊዜ ሮጧል።

➙ 2 ማይል 4 ጊዜ ሮጧል።

➙15 ኪሎ ሜትር ጎዳና 3 ጊዜ ሮጧል።

➙ ግማሽ ማራቶን 2 ጊዜ ሮጧል።

➙ አንድ ማይልን 10 ማይልን እና 25 ኪሎ ሜትርን አንድ አንድ ጊዜ ሮጧቸዋል።

ቀነኒሳ ካደረጋቸው ከ170 ውድድሮች ውስጥ

➢ 110 ውድድሮችን – ❶ኛ

➢ 21 ውድድሮችን – ❷ኛ

➢ 6 ውድድሮችን – ❸ኛ ሆኖ ጨርሷል።

ከ170 ውድድሮች ውስጥ 137 ውድድሮችን ሜዳሊያዎች ማለት ነው።

🇪🇹 35 ጊዜ ሀገሩን ወክሎ ያገኛቸው ድሎች

🥇 24 ወርቅ

🥈 5 ብር

🥉 1 ነሀስ

🇪🇹 ሜዳሊያዎቹ ሲዘረዘሩ

📌 በኦሎምፒክ

🥇 ❸ ወርቅ

🥈 ❶ ብር

👉 ❶ ዲፕሎማ ❹ኛ ደረጃ አግኝቶ

📌 በአለም አትሌትክስ ሻንፒዮና

🥇 ❺ ወርቅ

🥉 ❶ ነሀስ

📌 በአለም ሀገር አቋራጭ

🥇⓭ ወርቅ

🥈 ❶ ብር

📌 ወጣቶች ሻንፒዮና

🥈❷ ብር

📌 ኮንትኔታል

🥈 ❶ ብር

📌 በአፍሪካ ሻንፒዮና

🥇 ❸ ወርቅ

👉 ❶ ዲፕሎማ ❹ኛ ደረጃ አግኝቷል።

=====
🇪🇹 ቀነኒሳ እንዲህ ውጤቱ ያማረው የተለየ ፍጥረት ስለሆነ አይደለም።

📌 ስራውን ስለሚያከብር ስነ ስርዓት ያለው ለዓላማው የሚኖር ስፓርተኛ ስለሆነ ብቻ ነው።

📌 ቀነኒሳ በቀለ በፀባዩ የተመሰገነ ከስፓርት ሜዳ ውጪ የትም የማታየው ስነ ስርአት ያለው ስፓርተኛ ነው።

የሀገር ኩራታችን ብሄራዊ አርማችን

ክቡር ዶክተር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እንኳን ደስ ያለህ!!

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article”የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች ሥራ ፈላጊ ሳይኾኑ ሥራ ፈጣሪ መኾናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል” የደብረታቦር ከተማ ሥራና ስልጠና መምሪያ
Next article“ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት አስመጋቢዎች እንጂ ተመጋቢዎች አልነበርንም” ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ