”የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች ሥራ ፈላጊ ሳይኾኑ ሥራ ፈጣሪ መኾናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል” የደብረታቦር ከተማ ሥራና ስልጠና መምሪያ

52

ደብረታቦር: ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ደብረታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያና ቴክኒክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ደብረታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2015 የትምሕርት ዘመን በመደበኛውና በማታው፤ በአጫጭርና የረጅም ጊዜ መርሐ ግብር ሲያሰለጥናቸው የቆያቸውን 352 ሰልጣኞች አስመርቋል። ከተመራቂዎች መካከል 189 ሴቶች ናቸው።

የደብረታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተወካይ ዲን ክንዴ ጌታሁን እንዳሉት ኮሌጁ ለ4 ሺህ 864 ተማሪዎች በተለያዩ ዘርፎች አጫጭር ስልጠና መስጠቱን ገልጸዋል።

ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ ራሱን በማደራጀትና አቅሙን በማሳደግ ስልጠናዎችን ሲሰጥ እና ለተለያዩ ተቋማት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስረድተዋል።

የደብረታቦር ከተማ የሥራና ስልጠና መምሪያ ኀላፊና የደብረታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሥራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አባይ አለባቸው ” የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎች ሥራ ፈላጊ ሳይኾኑ ሥራ ፈጣሪ መኾናቸው ልዩ ያደርጋቸዋል” ብለዋል።

አቶ አባይ አክለውም ”ለሥራ የተፍታቱ እጆችና ዝግጁ የኾነ አዕምሮ ስላላችሁ በተማራችሁት ሙያ ወደሥራ በመግባት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የድርሻችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

3 ነጥብ 9 አጠቃላይ ውጤ በማስመዝገብ የተመረቀው ሙሉጌታ ኤፍሬም በአይ.ሲ.ቲ. ዘርፍ ጠንክሮ በመሥራት በሥራ ፈጠራ ሕይዎቱን ለመምራት ማሰቡን ተናግሯል።

በጋርመንት ዘርፍ በደረጃ 5 አጠቃላይ ውጤት 3 ነጥብ 93 በማስመዝገብ የተመረቀችው አየሁ ደሴ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፋ በመመረቋ ደስተኛ መኾኗን ገልጻለች። በቀጣይም የሚገጥማትን ፈተና በመቋቋም ሥራ ፈጥራ እንደምትሠራ ተናግራለች።

✍ደብረታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከተቋቋመበት ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ የዘንድሮውን ጨምሮ ለ26ኛ ጊዜ 27 ሺህ በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የተመረቃችሁት ለእውነት መታገል የኅልውና ጉዳይ በኾነበት ወቅት ነው” ፕሮፌሰር ከፍያለው ዓለማየሁ
Next articleአርሲ ዩኒቨርሲቲ ለአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የክብር ዶክትሬት ሰጠ።