
ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሙያ የጥንካሬ ተምሳሌትና በዘርፉ ለበርካቶች አርአያ ስለመኾኗ ተገቢ እውቅና ይኾን ዘንድ ነው ዩኒቨርሲቲው የዓመቱን የአርት የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የሰጣት ፡፡
በተመሳሳይ ለሆላንዳዊው ሄሪት ሆልት ላንድ በአትክልትና ፍራፍሬ ሰብል ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ዩኒቨርሲቲው የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 7 ሺህ 600 ተማሪዎችን አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የዮኒቨርሲቲው አመራሮች ተገኝተዋል። ከተመራቂዎች ውስጥ 2 ሺህ 235 የሚኾኑት ሴቶች መኾናቸው ተጠቅሷል።
ዩኒቨርሲቲው በእስካሁኑ የመማር ማስተማር ጉዞው ከ170 ሺህ በላይ ዜጎችን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አስልጥኖ ማስመረቁም ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!