ዶክተር ፍሬው ተገኝ ተመራቂ ተማሪዎች በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ኅብረተሰብ በቅንነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉ አሳሰቡ።

51

ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው እና በማታው መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን ከ7 ሺህ 6 መቶ በላይ ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 60 ዓመታት በርካታ ተማሪዎችን አስተምሮ ለልቀት አብቅቷል ተብሏል። የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ.ር) ተመራቂ ተማሪዎች በተማሩበት የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን ኀብረተሰብ በቅንነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉ መልዕክት አስተላለፈዋል።

ዩኒቨርስቲው ጎልማሳ ዩኒቨርስቲ በመኾኑ የአብራኩን ክፋዮች ለፍሬ እያበቃ ነው ብለዋል ፕሬዜዳንቱ። ለአጋርነት ሥለተመሠረትን በአጋርነት እንሠራለን ብለዋል። ዩኒቨርስቲው በእለቱ ለአንጋፋዋ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ እና ለጌሪት ሆልትላንድ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ውድ ተመራቂዎቻችን ባገኛችሁት እውቀት ሕዝባችሁንና የጋራ ቤታችሁን ኢትዮጵያን እንድታገለግሉ፣ እንድትጠብቁም አደራ እላለሁ” ዶክተር ታምሬ ዘውዴ
Next articleየደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በቡሬ ካምፓስ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።