የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ።

82

ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሀገሪቱ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት በተለይም ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች ባገኙት ገንዘብ 27 ሁለተኛና አዳሪ ትምህርት ቤቶችን አስገንብተዋል።

ትምህርት ቤቶቹ በርካታ ተማሪዎች መቀበል አንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን ትምህርት ቤቶቹም ደረጃቸውን የጠበቁ መሆኑን ኢዜአ በዘገባው አመላክቷል።

ትምህርት ቤቶቹ በበአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በአዲስ አበባ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ክልሎች መገንባታቸውም ታውቋል።

የክብር ዶክተሬቱም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በትምህርትና በሰብዓዊ ልማት ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክተሬቱ እንደተሰጣቸው ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጀማ ወንዝ የብረት ድልድይ እንደገና ተሠርቶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
Next article“ማንኛውም ስኬት የሚገኘው ፈተናን ተጋፍጦ በማለፍ ብቻ ነው” ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)