
ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በቅርቡ 60ኛ ዓመቱን በድምቀት ያከበረው አንጋፋው የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ.ር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተማራቂ ተማሪ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!