
ደሴ: ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ለዓመታት ተማሪዎችን ሲያስተምር የቆዬው መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለአራተኛ ጊዜ ነው ተማሪዎችን እያስመረቀ የሚገኘው፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ከፍያለው ዓለማየሁ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ታምሬ ዘውዴ (ዶ.ር) ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!