
ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የክረምት ወቅታዊ የግብርና ሥራዎችን አስመልክቶ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ኃይለማሪያም ከፍያለው (ዶ.ር) የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም ለግብርና ሥራ ችግር መኾኑን አንስተዋል። የቀረበውን ግብዓት ለማዳረስም አልፎ አልፎ በክልሉ በሚፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የስርጭት ችግር ማጋጠሙን ያነሱት ኀላፊው ችግሩን ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ አሳስበዋል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱ ሁሴን ግብርናውን ለማሳደግ የቀረበውን ግብዓትና ቴክኖሎጅ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል። በክረምቱ በወቅት የተባይ አሰሳ፣ አረምን በወቅቱ በማረም እና የተጀመረውን አረንጓዴ አሻራ ልማት በተለይም ደግሞ ለአትክልትና ፍራፍሬ ትኩረት በመሥጠት የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!