
ባሕር ዳር: ሐምሌ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶችን የ2016 ዓ.ም በጀት እና የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን፣ የአማራ ክልል ምክር ቤትን የ2016 ዓ.ም በጀት መርምሮ አጽድቋል።
በዚህ መሠረትም የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የ2016 ዓ.ም በጀት 2 ቢሊዮን 64 ሚሊዮን 542 ሺህ 247 ብር ኾኖ ሲጸድቅ፣ የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የ2016 ዓ.ም በጀት የመደበኛና የካፒታል በጀት 76 ሚሊዮን 466 ሺህ 425 ብር ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት የ2016 ዓ.ም በጀት ለሥራ ማስኬጃና ለደመወዝ 58 ሚሊዮን 384 ሺህ 465 ብር ኾኖ ጸድቋል።
ዘጋቢ:-ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!