የአማራ ክልል የ2016 በጀት ዓመት ጠቅላላ በጀት 137 ቢሊዮን 408 ሚሊዮን 472 ሺህ 187 ኾኖ ጸደቀ።

78

ባሕር ዳር: ሐምሌ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት በ2016 በጀት ዓመት ጥቅል የበጀት ጣራ አመዳደብ ላይ መክሮ የበጀት ዓመቱን የልማት ሥራዎች ማስፈጸሚያ ጠቅላላ በጀት አጽድቋል።

አጠቃላይ በጀቱም: 137,408,472,187 (አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ቢሊዮን አራት መቶ ስምንት ሚሊዮን አራት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሰባት ብር) ኾኖ በምክር ቤቱ ጸድቋል።

የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ጥላሁን መሃሪ የ2016 በጀት ዓመት የክልሉ በጀት ዋነኛ ምንጮች ከክልሉ ታክስ እና ታክስ ያልኾኑ ገቢዎች የሚሰበሰብ እና ከፌዴራል መንግሥት ድጋፍ የሚገኝ ነው ብለዋል።

ከ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት ውስጥ:-

👉 89 ቢሊዮን 279 ሚሊዮን 467 ሺህ የሚኾነው በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ

👉 44 ቢሊዮን 519 ሚሊዮን 851 ሺህ 979 የሚኾነው ከፌደራል መንግሥት ጥቅል የቀመር መደበኛ ድጋፍ ድርሻ

👉3 ቢሊዮን 24 ሚሊየን የሚኾነው ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ከፌደራል መንግሥት ድጋፍ እና

👉 585 ሚሊዮን 153 ሺህ 208 የሚኾነው ከውጭ እርዳታ የሚገኝ ስለመኾኑ የገንዘብ ቢሮ ኀላፊው ተናግረዋል።

የተበጀተው በጀት በ2015 በጀት ዓመት ከተመደበው አንጻር ሲታይ የ42 ቢሊዮን 88 ሚሊዮን 352 ሺህ 585 ብር እድገት እንዳለው ያሳያል።

ዶክተር ጥላሁን ማንኛውም የፋይናንስ ሥርዓቱ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ባለበት አካሄድ እንዲመራ የክልሉ መንግሥት እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ በመቀጠል በጀቱ የታለመለትን የልማች ግብ እንዲመታ ማስቻል እንዳለበትም ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ ናት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
Next articleየ2016 ዓ.ም በጀትን ለታለመለት ዓላማ በአግባቡ ማዋል እንደሚገባ ርእሰ መሥተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አሳሰቡ፡፡