
ባሕር ዳር: ሐምሌ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ዋንግ ዪ ጋር ተወያይተዋል።
ዋንግ ዪ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ የተላከ መልዕክትም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!