
ባሕር ዳር: ሐምሌ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ዋንግ ዪ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋንግ ዩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል።
በቆይታቸውም ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የኢትዮጵያና የቻይና ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነት የበለጠ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉም ተብሏል።
ኃላፊው ቀደም ሲል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!