
ባሕር ዳር: ሐምሌ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ የአማራ ክልል መንግሥት የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመንግሥት ሥራዎች ማስፈጸሚያ ተጨማሪ በጀት ለማጽደቅ የወጣውን አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።
ተጨማሪ በጀቱም 1 ቢሊዮን 72 ሚሊየን 746 ሺህ124 ብር በተጨማሪ በጀትነት ሥራ ላይ ውሏል ተብሎ ጸድቋል።
በተያያዘም ምክር ቤቱ የአማራ ክልል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን ተግባርና ኃላፊነት መወሰኛ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ምርምሮ አጽድቋል።
ዘጋቢ:-ጋሻው አደመ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!