የአማራ ክልል ምክር ቤት የሶስተኛ ቀን ጉባዔውን ጀምሯል።

26

ባሕር ዳር: ሐምሌ 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከሐምሌ 12 እስከ 14/2015 ዓ.ም የሚካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባዔ የሶስተኛ ቀን ጉባዔ ተጀምሯል።

በምክር ቤቱ የጠዋት መርሃ ግብር በትናንትናው ዕለት ያዳመጠውን የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶችን የ2015 በጀት ዓመት የ11 ወር እቅድ አፈጻጸም ውሎ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ በዛሬው የ6ኛ መደበኛ ጉባዔው ማጠቃለያ ቀን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔዎችንም ያሳርፋል፣ የተለያዩ ሹመቶችንም መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። በዕለቱ ከሚመክርባቸው ጉዳዮች መካከል:-

👉የአማራ ክልል ዋና ኦዲት መሥሪያ ቤትን ተግባርና ኀላፊነት መወሰኛ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ መርምሮ ማጽደቅ

👉የአማራ ክልል የ2016 በጀት ዓመት ጥቅል የበጀት ጣሪያ አመዳደብ እና የወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የድጎማ በጀት ቀመር እና የ2016 በጀትን ለማጽደቅ የበጀት አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅን መርምሮ ማጽደቅ

👉 የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት በጀትን መርምሮ ማጽደቅ

👉 የክልሉን ኦዲት መሥሪያ ቤት የ2016 በጀት ዓመት በጀቱን መርምሮ ያጸድቃል

👉የምክር ቤቱን የ2016 በጀት ዓመት በጀቱን መርምሮ ማጽደቅ እና

👉 ልዩ ልዩ ሹመቶችን መርምሮ ማጽደቅ በ6ኛ መደበኛ ጉባዔ የሦስተኛ ቀን የምክር ቤቱ ውሎ የሚጠበቁ ጉዳዮች ናቸው።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ሕዝብ መሰረታዊ የኾኑ የማንነት ጥያቄዎች በሕግ የጸኑ እንዲኾኑ ተጠየቀ።
Next articleየአማራ ክልል ሕዝብ መሰረታዊ የኾኑ የማንነት ጥያቄዎች በሕግ የጸኑ እንዲኾኑ ተጠየቀ።