ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ፡፡

82

ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ ለ15ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ሲያስተምራቸው የነበሩ ከ2ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ ለተመራቂ ተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት“ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ያገኛችሁትን ዕውቀት እና ከወላጆቻችሁ ያገኛችሁትን ቅን ልቦና በመጠቀም ማኅበራዊ ኀላፊነታችሁን በተገቢው መንገድ መወጣት ይገባችኋል” ብለዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ተገኘወርቅ ጌጡ ተመራቂ ተማሪዎች ለአላማችሁ በመፅናት በተለያዩ ችግሮች እየተሰቃዩ ያስተማሯችሁን ወገኖች ውለታ መመለስ አለባችሁ ብለዋል።

የዋንጫ ተሸላሚ ተመራቂ ተማሪዎች በቀጣይ ባገኙት ዕውቀት ሀገርና ሕዝብን ሊጠቅም የሚችል ሥራ ለመሥራት መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የዩኒቨርሲቲው መምህራንን በ3ኛ ዲግሪ አስመርቋል፡፡

በኦስትሪያ ቦኩ ዩኒቨርሲቲ መምህር ለኾኑትና በ2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የመሬት አሥተዳደር ትምህርት ክፍል እንዲቋቋም ለትምህርት ክፍሉ ሙሉ የላብራቶሪ እቃ እንዲሟላ እና የትምህርት ክፍሉ መምህራን አጫጭር ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ሲያደርጉ ለነበሩት ለፕሮፌሰር ሬይንፈሬድ ማንስበርግ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡

ዘጋቢ፡- ንጉስ ድረስ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በበጀት ዓመቱ ከ674 ሺህ በላይ መዝገቦች እልባት አግኝተዋል” ጠቅላይ ፍርድ ቤት
Next articleበተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል።