“ለተመራቂዎች በሙሉ ፍሬያማ ህይወት እንዲገጥማችሁ እመኛለሁ” አቶ ደመቀ መኮንን

67

ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የምረቃ በዓላቸውን ላካሄዱ እንዲሁም በዝግጅት ላይ ላሉ ተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አቶ ደመቀ በመልእክታቸው፤ ተመራቂዎች በሙሉ ከብዙ ጥረት በኋላ ላሳካችሁት ግብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ተመራቂዎችን ለዚህ ክብር ለማብቃት ወልዳችሁ ለፍታችሁ ያሳደጋችሁ ወላጆች እንዲሁም በርትታችሁ ያስተማራችሁ መምህራን እንኳን ፍሬያችሁን ለማየት አበቃችሁ ሲሉም ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት፤ “እኔም በተማርኩበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተምራ ከጥቁር አንበሳ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪ በፋርማሲ የተመረቀችውን ልጄን ደስታ ለመካፈል ከቤተሰቦቼ ጋር በምረቃ በዓሉ በመታደሜ ደስታዬ ልዩ ነው” ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአዕምሮ ውስንነት ያለባቸው ልጆችን ችግር ለመቅረፍ እንሠራለን” የአማራ ክልል የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች ማኅበር አባላት
Next articleየልማት ተነሽ አርሶ አደሮች ተገቢውን ካሳ በወቅቱ እንዲያገኙ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ(ዶ.ር) ገለጹ።