
ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አርቲስት እጅጋየው ሽባባው መልእክት እንዳለችው በተሰጣት የክብር ዶክትሬት መደሰቷን ገልጻለች፡፡
አርቲስት እጅጋየው ሽባባው በሀገሯ ለክብር ዶክትሬት መታጨት በራሱ ትልቅ ደስታ እንደሚፈጥር ገልጻ ለክብሩ ከመታጨት አልፋ የክብር ዶክትሬቱን በማግኘቷ ያከበራትን የሀገሯን ሕዝብ አመሥግናለች፡፡
“እምየ ሀገሬ ኢትዮጵያ ሳይገባኝ የሰጠችኝን የክብር ዶክትሬት ባይገባኝም ከፍቅራችሁ ሁኔታ የሰጣችሁኝ በመኾኑ ምሥጋናየ ከፍ ያለ ነው” ብላለች፡፡
ፈጣሪ ሲፈቅድ በአካል ተገኝታ የናፈቃትን ሀገሯን እንደምታይም ያላትን ተስፋ ተናግራለች፡፡
አርቲስት እጅጋየው ሽባባው ፈጣሪ ሀገሯን እና ሕዝቡን እንዲጠብቅ ያላትን ፍላጎት እና ምኞትም ገልጻለች፡፡
በምሥጋናው ብርሃኔ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
