“እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኾነውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ነው ለአርቲስ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የሰጠ” የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጋርዳቸው ወርቁ

64

ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጋርዳቸው ወርቁ በስነ ሥርአቱ ላይ እንዳሉት የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የሰጠው የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ የመጀመሪያ ነው ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የክብር ዶክትሬት ዲግሪ መስጠቱ ጂጂን ማክበር ጥበብን ማክበር፣ የኢትዮጵያን ታሪክ እና ጀግኖችን ማክበር፣ ፍቅርን ፣ አንድነትን ፣ ሰላምን፣ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ማክበር መኾኑን በመረዳት እንደኾነ ተገልጿል፡፡

ታላቋ ድምጻዊት እና ባለቅኔዋ ጂጂ በሥራዎቿ የአኹኑ ትውልድ በድህነት እና በዘረኝነት ላይ እንዲዘምት፣ እንዲጠላ ቀድማ ያሳሰበች እና የታገለች ድንቅ አርቲስት መኾኗም ተገልጿል፡፡ ለኢትዮጵያ ሰላም እና አንድነት አጥብቃ መቀኘቷም በመድረኩ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያን እና አፍሪካን በዓለም መድረክ በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ማስተዋወቋም ተገልጿል፡፡

የእንጅባራ የኒቨርሲቲ ለእጅጋየሁ ሽባባው ያበረከተውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ወላጅ እናቷ ወይዘሮ ተናኘ ስዩም በመድረኩ ተገኝተው ተቀብለዋል፡፡ እናቷ ወይዘሮ ተናኘ ልጃቸው ጂጂ ከልጆቻቸው የተለየ ስጦታ የታደላት መኾኗን ተናግረዋል፡፡ ልጃቸውን ዩኒቨርሲቲው አክብሮ ለሰጣት የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በልጃቸው እና በቤተሰቦቻቸው ስም አመስግነዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ፋሲካ ዘለዓለም

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከክልሎች ሆስፒታሎች የተውጣጡ የሥራ ኀላፊዎችና ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የጤና ኤግዚቢሽን ጎበኙ።
Next article“አክብራችሁ የሰጣችሁኝ የክብር ዶክትሬት በጣም አስደስቶኛል” አርቲስት እጅጋየው ሽባባው