ከክልሎች ሆስፒታሎች የተውጣጡ የሥራ ኀላፊዎችና ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የጤና ኤግዚቢሽን ጎበኙ።

22

ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አየለ ተሾመ (ዶ.ር) ኤግዚቢሽኑ እንደሀገር ከዚህ ቀደም ያልተጠቀምንበትን ሀገር በቀል የመድኃኒት መቀመሚያዎችን ከሳይንሳዊው ሕክምና ጋር በማዋሀድ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የቀረቡበት ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው በጤናው ዘርፍ ያሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በዲጂታል መንገድ ዘምነው የቀረቡበት ኤግዚቢሽን ስለመኾኑም አስረድተዋል፡፡

ኤግዚቢሽኑ ከላይ ጀምሮ በተዋረድ መተግበር ያለበት በመኾኑ የክልል ጤና ተቋማት ልምድ እንዲወስዱበት ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ስለመኾኑም ጠቅሰዋል።

ከተለያዩ የክልል ሆስፒታሎች መጥተው የጤና ሚኒስቴር በሳይንስ ሙዚየም ያዘጋጀውን ኤግዚቢሽን ሲጎበኙ አሚኮ ያነጋገራቸው የሥራ ኀላፊዎችም ጉብኝቱ ልምድ የቀሰሙበትና ወደ ጤና ተቋሞቻቸው ሲመለሱ ጥራቱን የጠበቀ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መኾኑን ገልጸዋል፡፡

መሰል የልምድ ልውውጥ ማድረግ የሚያስችሉ ጉብኝቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ መዘጋጀታቸው ሚናው የጎላ በመኾኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዩኒቨርሲቲዎቻችን የሕዝባችንን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ መኾን አለባቸው” ፕሬዚደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ
Next article“እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኾነውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ነው ለአርቲስ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የሰጠ” የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጋርዳቸው ወርቁ