ለመቄዶኒያ መስራቹ ቢኒያም በለጠ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጠ።

104

ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቢኒያም በለጠ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በማታና በርቀት ትምህርት መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 8 ሺህ 642 የቅድመ ምረቃና ድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን በሚሊኒየም አዳራሽ እያስመረቀ ነው።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

በስነ-ሥርዓቱ ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማኅበር መስራችና ሥራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠ የክብር ዶክትሬት ማበርከቱን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለሰላም እና መቻቻል ጠንክራችሁ ሥሩ” ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ
Next article“ዩኒቨርሲቲዎቻችን የሕዝባችንን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ መኾን አለባቸው” ፕሬዚደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ