
እንጅባራ: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ.ር) ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያገኙትን ጥበብ፣ የአላማ ፅናትና ጥንካሬ በመጠቀም ሕዝቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ አሳሰበዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው 750 ተመራቂዎችን ማስመረቁንም ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በመማር ማስተማር እንዲሁም በጥናትና ምርምር መጠነ ሰፊ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
በዩኒቨርሲቲው የምረቃ ሥነ ሥርዐት ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የዩኒቨርሲቲው የክብር እንግዳ ፕሮፌሰር ጌትነት ታደለ “የእናንተ መመረቅ የኢትዮጵያ መመረቅ ነው ብለዋል፡፡
ፕሮፌሰር ጌትነት ተመራቂዎች በሥራዎቻችሁ ሁሉ ኢትዮጵያን በማስቀደም ሥሩ ሲሉም ነው ያስገነዘቡት፡፡
“ለሰላም እና መቻቻል ጠንክራችሁ ሥሩ” ያሉት ፕሮፌሰር ጌትነት እያንዳንዱ በተፈጥሮ የተሰጠውን ጥንካሬ፣ ማኅበረሰባዊና ሙያዊ ግዴታ እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!