“በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በአጼ ተዎድሮስ ስም በተሠራው ሮኬት የተደረገው የተሳካ ሙከራ ኢትዮጵያን በህዋ ምህንድስና ስሟ እንዲጠራ ያደረገ ነበር” አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ.ር)

33

ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በጋፋት የህዋ ምህንድስና ማእከል በአጼ ቴዎድሮስ ስም በተሠራው ሮኬት የተደረገው የተሳካ ሙከራ ኢትዮጵያን በህዋ ምህንድስና ስሟ እንዲጠራ ያደረገ እንደነበር የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ.ር) ገለጹ።

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዐቱ ላይ የተገኙት የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘ እና ተባብሮ እየሠራ ያለ ስለመኾኑም አስገንዝበዋል፡፡

በዚህ ዓመት ከ71 በመቶ በላይ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አስፈትኖ ያሳለፈው ዩኒቨርሲቲው በዚህ ሂደት አልፈው ለምረቃ የበቁ ተማሪዎችን እንኳን ደሳላችሁ ብለዋል፡፡

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተካሄደው የመውጫ ፈተና አልፈው ለምረቃ የበቁ ተመራቂዎች ሀገራቸው ከገባችበት ችግር ለማላቀቅ ሀገራቸው ተስፋ እንዳደረገችባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በየጊዜው አቅሙን እያሳደገ የመጣ ዩኒቨርሲቲ ስለመኾኑም አብራርተዋል፡፡

በቴክኖሎጅ፣ በጤና እና በግብርና የላቀ ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ እንደኾነም አስገንዝበዋል፡፡

የኅብረተሰቡን የትምህርት ፍላጎትን ለማሟላት ዩኒቨርሲቲው የትምህርት የልህቀት ማእከል እያስፋፋ እንደሚገኝም ነው ፕሬዚዳንቱ የገለጹት፡፡

ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የሜካናይዜሽን ሥራን ለኅብረተሰቡ እያስተዋወቀ እንደሚገኝ ያስረዱት ዶክተር አነጋግረኝ የተሻሻሉ የዘር ማሻሻል ሥራም ሲሠራ እና ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ሲያደርግ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው፦

👉ዘመናዊ የሕክምና ሥርአት እንዲኖር፣

👉በበጋ ታዳጊዎችን በአይሲቲ ብቁ እንዲኾኑ የማድረግ ተግባር፣

👉የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታማ እንዲኾኑ የማድረግ ሥራ ሲያከናውን መቆየቱንም አስገንዝበዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ ዩኒቨርሲቲው በጋፋት የህዋ ምህንድስና አማካኝነት አጼ ቴዎድሮስ በሚል የተሠራው ሮኬት የተሳካ ሙከራ ማድረግ መቻሉ የዩኒቨርሲቲውን እውቅና ከፍ ያደረገ ስለመኾኑም ነው የተናገሩት፡፡ ሥራው ከዩኒቨርሲቲው በዘለለ ኢትዮጵያ በህዋ ምህንድስና ስሟ እንዲጠራና አንድ ምዕራፍ ከፍ ያደረጋት ተግባር መኾኑንም አብራርተዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ምሥጋናው ብርሃኔ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና ተከታታይ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች ለ4ኛ ዙር እያስመረቀ ነው።
Next articleእንጅባራ ዩኒቨርሰቲ በመጀመሪና ሁለተኛ ዲግሪ 750 ተመራቂ ተመሪዎችን አስመረቀ።