
ደባርቅ: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ)ዩኒቨርሲቲው በ 4 ኮሌጆች በ 21 የትምህርት ክፍሎች በመደበኛ የትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች ለ4ኛ ዙር ነው እያስመረቀ የሚገኘው።
በዕለቱ በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸው የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪዎቹንም እያስመረቀ መኾኑን ከዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ የኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ካውንስል አባል እና ሲኒየር ተመራማሪ እና የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዓለማየሁ ቢሻው (ፕሮፌሰር)፤ የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ (ዶ.ር)፤ የአማራ ክልል የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ሴክሬታሪያት አስማረ ደጀን (ዶ.ር)፤ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት መስራች አበጀ ታፈረ (ዶ.ር)፤ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው የአሥዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት መስራች አወቀ በላይ (ዶ.ር) እና ሌሎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:-አድኖ ማርቆስ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!