የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በማታ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን ከ2 ሺህ 100 በላይ ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል።

28

ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ለ15ኛ ዙር፤ በማታ መርሐ ግብር ደግሞ ለ13ኛ ዙር ያሠለጠናቸውን 2 ሺህ143 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በ1ኛ ዲግሪ 1 ሺህ 692፤ በ2ኛ ዲግሪ 448፤ በ3ኛ ዲግሪ 3 ተማሪዎችን በዛሬዉ እለት የሚያስመርቅ ይሆናል።

የዩኒቨርሲቲው ኘሬዚዳንት ዶክተር ንጉሥ ታደሰ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተቀመጠው አሠራር መሰረት የመውጫ ፈተና የተሰጠበት ወቅት በመኾኑ ምርቃቱን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ለአለም ለይኩን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ምክር ቤት የ6ኛ መደበኛ ጉባኤውን የሁለተኛ ቀን ውሎ ጀምሯል።
Next articleደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና ተከታታይ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች ለ4ኛ ዙር እያስመረቀ ነው።