
ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ከሐምሌ 12 እስከ 14/2015 ዓ.ም የሚካሄደውን 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን ውሎውን ጀምሯል። በመጀመሪያ ቀን የምክር ቤቱ ውሎ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የክልሉን አስፈጻሚ አካላት እቅድ አፈጻጸም የተጠቃለለ ሪፖርት አቅርበው ጥያቄና አስተያየቶች ከአባላቱ እየቀረቡ ነበር።
ከምክር ቤት አባላት የሚቀርቡ ጥያቄ እና አስተያየቶች በዛሬ ጥዋት የምክር ቤቱ መርሐ ግብርም ቀጥለዋል።
ከአስተያየት እና ጥያቄዎች በኋላ አስፈጻሚ አካላት ተጨማሪ ማብራሪያ እና ምላሾችን እንደሚሰጡም ይጠበቃል። በምክር ቤቱ ውሎ የሚነሱ ዋና ዋና ጉዳዮችን አሚኮ ኦንላይን ለተከታታዮቹ ያደርሳል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!