
ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የአርት የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰጣት በሙሉ ድምጽ ማፅደቁ ይታወቃል።
አርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው “ጂጂ” የሀገር ፍቅርን የተላበሱ የኪነ ጥበብ ሥራዎቿን ለአድማጭ አበርክታለች።
በተለይ የሀገሯን ባህልና ሙዚቃ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማስተዋወቅ ረገድ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፋለች፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት በመደበኛ ትምህርት መርሃ ግብር በስድስት ኮሌጆች በ27 ትምህርት ፕሮግራሞች እና በድኅረምረቃ ትምህርት ሦስት ፕሮግራሞች ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!