እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ሠልጣኝ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

58

ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው መርሐ ግብር በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ ያስመርቃል።

ዩኒቨርሲቲው ለ4ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን ከ900 በላይ ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ ዛሬ እንደሚያስመርቅ በወጣው መርሐ ግብር ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በመደበኛ መርሐ ግብር በ3 የትምህርት ክፍሎች ያሠለጠናቸውን የሁለተኛ ዲግሪ እና ለ4ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎችን እንደሚያስመርቅ መርሐ ግብሩ ያሳያል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው “ጂጂ” የክብር ዶክትሬት ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል።

በሥነ ሥርዓቱ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና የተማሪ ወላጆች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው
📸 የአዊ ኮሙኒኬሽን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ወልቃይት ከነጻነት ወደ ልማት ተሸጋግሯል” የወልቃይት ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ክብረአብ ስማቸው
Next articleለአርቲስት እጅጋየሁ ሽባባው የአርት የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ በዛሬው ዕለት ይከናወናል።