
ባሕር ዳር: ሐምሌ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት የሚያስተዋውቅ ሴሚናር በቻይና ቤጂንግ እየተካሄደ ነው።
ሴሚናሩን ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ጋር በመተባበር ነው።
በሴሚናሩ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ተቋማት የተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የሴሚናሩ ዋና አላማም የኢንቨትመንት ዘርፉን ከማስተዋወቅ አኳያ በቂ የሆነ ግንዛቤን ማዳበር፣ በፌዴራል፣ በክልል እና ከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት አካላት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት ፣በማደግ ላይ ባሉ አገራት መካከል ዓለም አቀፋዊ የትብብር መድረክን መፍጠር እንዲሁም በኢንቨስትመንትና ንግድ ፕሮሞሽን የልምድ ልውውጥ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!