
“ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን እህትማማችነት እና ወንድማማችነት የበለጠ ለማጎልበት አጠናክረን እንቀጥላለን” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
ባሕር ዳር: ሐምሌ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የክልሉን የ2015 በጀት ዓመት የሰላም እና የልማት ሥራዎች በምክር ቤቱ ጉባዔ ላይ አንስተዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ በበጀት ዓመቱ በልማትም ይሁን በጸጥታው ዘርፍ ወሳኝ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል። የክልሉ ሕዝብ የራሱን እና የአካባቢውን ሰላም እና ደኅንነት ለማስከበር ከመንግሥት እና ከጸጥታ መዋቅሩ ጎን ተሰልፎ ሲሠራ መቆየቱን የጠቆሙት ርእሰ መሥተዳድሩ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።
ዶክተር ይልቃል የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኃላ በሙሉ አቅም ወደ ልማት በመግባት ድህነትን ለመቀነስ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
ርእሰ መሥተዳድሩ ሰላማዊ ሂደቱን ለማጠናከር የተጀመረውን የአመራር ለአመራር ግንኙነት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። “ከሁሉም አጎራባች ክልሎች ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ እህትማማችነትና ወንድማማችነትን የበለጠ ለማጎልበት አጠናክረን እንቀጥላለን” ሲሉም ዶክተር ይልቃል በጉባዔው ላይ ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!