በአማራ ክልል 35 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) አስታወቁ፡፡

37

ባሕር ዳር: ሐምሌ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በ2015 በጀት ዓመት 42 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ሰፊ እንቅስቃሴ ሲደረግ የቆየ ሲኾን የገጠሙ ተግዳሮቶችን ሁሉ በመቋቋም እስከ ሰኔ መጨረሻ ድረስ 35 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ዶክተር ይልቃል አስታውቀዋል።

ይህ ገቢ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻደር የ10 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወይም የ40 በመቶ እድገት አለው። ለዚህ ውጤት መገኘት በሕገ ወጥ ደረሰኝ ላይ ጠንካራ ቁጥጥር መደረጉ፣ የኦዲት ውጤታማነትና ግብይታቸውን በሚደብቁ ግብር ከፋዮች ላይ የተሠራው ከፍተኛ የኾነ የቁጥጥር ሥራ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበራቸው ብለዋል።

በቀጣይም ማኅበረሰቡ ለሚገዛው ዕቃ ወይም አገልግሎት ደረሰኝ የመቀበል ባሕሉን በማሳደግ ለክልሉ ገቢ ማደግ የበኩሉን መወጣት አለበት ሲሉ ርእሰ መሥተዳድሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአስቸጋሪ ኹኔታዎች ውስጥ ኾነንም የተሻለ የልማት እና የኢኮኖሚ ለውጥ አስመዝግበናል” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)
Next articleበአማራ ክልል 35 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) አስታወቁ፡፡