“በአስቸጋሪ ኹኔታዎች ውስጥ ኾነንም የተሻለ የልማት እና የኢኮኖሚ ለውጥ አስመዝግበናል” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

78

ባሕር ዳር: ሐምሌ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ)ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የክልሉን አስፈጻሚ አካላት እቅድ አፈጻጸም የተጠቃለለ ሪፖርት በምክር ቤቱ ጉባዔ አቅርበዋል።

በ10 ዓመቱ ክልላዊ እቅድ መጨረሻ ድህነትን ወደ 10 በመቶ ለመቀነስ እና ክልላዊ የምርት እድገት 8 ነጥብ 3 እንዲያድግ በእቅድ ተይዞ እንደነበር ገልጸዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ እንደሀገር በርካታ ተግዳሮቶች በመግጠማቸው ሰላማችን፣ ኢኮኖሚያችን፣ ልማታችን እና የማኅበረሰባችን ሕይወት በእጅጉ የተፈተነበት ወቅት ነውም ብለዋል።

በአንድ በኩል ልማታችን እንዳይስተጓጎል፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሰላም እጦት የፈጠረውን ተግዳሮት ለመቋቋም ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ነው ያሉት። “በአስቸጋሪ ኹኔታዎች ውስጥ ኾነንም የተሻለ የልማት እና የኢኮኖሚ ለውጥ አስመዝግበናል” ሲሉም ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል።

ኢኮኖሚው ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በኮሮና፣ በአንበጣ ወረራ፣ ጎርፍና ድርቅ፣እንዲሁም በጦርነት የተፈተነ ቢኾንም በ2014 ዓ.ም የአማራ ክልል ጥቅል ምርት ከ5 ነጥብ 1 በመቶ በላይ እድገት አስመዝግቧል ነው ያሉት።

የውስጥ አንድነት እና ሰላማችንን ለማጠናከር ሁላችንም ከተረባረብን በቀጣይ ዓመታት የክልሉ ኢኮኖሚ የበለጠ እና ተጨባጭ እድገት ያስመዘግባል ሲሉም ዶክተር ይልቃል ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፈር ማዳበሪያ እጥረት ችግርን ለማቃለል 77 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ተናገሩ።
Next articleበአማራ ክልል 35 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) አስታወቁ፡፡