የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ችግርን ለማቃለል 77 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ተናገሩ።

74

ባሕር ዳር: ሐምሌ 12/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ከሐምሌ 12 እስከ 14/2015 ዓ.ም በሚያካሄደው 6ኛ ዙር፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የ2015 በጀት ዓመት ዋና ዋና የሴክተር መሥሪያ ቤቶችን የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ የግብርናውን ዘርፍ የሥራ እንቅስቃሴ ሲያብራሩ በ2015/2016 የምርት ዘመን በዘር ለመሸፈን ከታቀደው 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታሩ እስካሁን ታርሷል ብለዋል።

370 ሺህ ሄክታሩ ደግሞ እስከ ሐምሌ/2015 ዓ.ም ድረስ በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ በምርት ዘመኑ የክልሉ አጠቃላይ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት እቅድ 9 ሚሊዮን 500 ሺህ መኾኑን ገልጸዋል።

እስከ ሐምሌ/2015 ዓ.ም ድረስ 3 ሚሊዮን 350 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለስርጭት ቀርቦ 2 ሚሊዮን 899 ሺህ ኩንታሉ ለአርሶ አደሮች መሰራጨቱንም አንስተዋል።

እንደ ሀገር የገጠመውን የአፈር ማዳበሪያ እጥረት ችግር ለማቃለል 80 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ 77 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የሚኾን መዘጋጀቱን ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ ከግጭት ወደ ሰላም የመጣችበት አካሔድ ለአፍሪካ ምሳሌ እንደሚኾን የአፍሪካ ኀብረት የአስፈጻሚዎች ጉባኤ ማሳወቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
Next article“በአስቸጋሪ ኹኔታዎች ውስጥ ኾነንም የተሻለ የልማት እና የኢኮኖሚ ለውጥ አስመዝግበናል” ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)