ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ለአዲሱ የሰሜን ጎጃም ዞን አሥተዳድር አመራሮች ሹመት ሰጡ።

144

ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ለአዲሱ የሰሜን ጎጃም ዞን አሥተዳድር ለ23 አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል።

#በዚህ መሠረት፦

1. አቶ ነጋልኝ ተገኘ መለሰ የሰሜን ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣
2. አቶ ደሳለኝ ዳምጤ ደምሴ የሰሜን ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ፣
3. አቶ አዲሱ ማስረሻ ምናለ የሰሜን ጎጃም ዞን ውሃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ፣
4. አቶ የረጋ አለማየሁ ወርቁ የሰሜን ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ፣
5. አቶ መኳንንት ልጃለም መንገሻ የሰሜን ጎጃም ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ
6. አቶ አንተነህ ወንዱ በላይ የሰሜን ጎጃም ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ፣
7. አቶ ሹምበላይ ጠናው ውብአንተ የሰሜን ጎጃም ዞን መሬት መምሪያ ኃላፊ፣
8. አቶ ደረስ ክንዱ አሞኘ የሰሜን ጎጃም ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ፣
9. አቶ አንዷለም ፈንቴ ይራድ የሰሜን ጎጃም ዞን መስኖና ቆላማ አካባቢዎች መምሪያ ኃላፊ፣
10. አቶ ገብረስላሴ ታዘብ ካሳ የሰሜን ጎጃም ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ፣
11. ወይዘሮ በቀለች መልካሙ ተገኘ የሰሜን ጎጃም ዞን ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ፣
12. ወይዘሪት የሩቅሰው ይታይህ ታፈረ የሰሜን ጎጃም ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ፣
13. ወይዘሪት ትርንጎ እንየው አያሌው የሰሜን ጎጃም ዞን ወጣትና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ፣
14. ወይዘሪት ምትኬ ባዩ ውድነህ የሰሜን ጎጃም ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ፣
15. አቶ ቴዎድሮስ መስፍን አረጋ የሰሜን ጎጃም ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ፣
16. አቶ አንተነህ አዳሙ ደምለው የሰሜን ጎጃም ዞን እንስሳትና ዓሳ ሃብት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ፣
17.አቶ አምሳሰው አቸነፍ በሌ የሰሜን ጎጃም ዞን ህብረት ስራ ማህበራት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ፣
18. ወይዘሪት አንሻ ደሳለኝ አስፋው የሰሜን ጎጃም ዞን የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ኃላፊ፣
19. አቶ መልካሙ አልከኝ አቤልነህ የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ፣
20. ኢ/ር ተበጀ ደሴ አለሙ የሰሜን ጎጃም ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ፣
21. ወይዘሪት ነጻነት ሲሳይ ገብሬ በምክትል መምሪያ ኃላፊ ደረጃ የሰሜን ጎጃም ዞን ሕዝብ ግንኙነት ረዳት አማካሪ፣
22. አቶ ታከለ ሙሉጌታ አድማሱ በምክትል መምሪያ ኃላፊ ደረጃ የሰሜን ጎጃም ዞን የህዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት ረዳት አማካሪ፣
23 ወይዘሪት ሀይማኖት ድረስ ዋሴ በምክትል መምሪያ ኃላፊ ደረጃ የሰሜን ጎጃም ዞን ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሴቶች ጉዳይ አማካሪ ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥተዋል።

መረጃው የአብክመ ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ነው።

Previous article“ዝቅተኛ የጤና መድኅን አገልግሎት አጠቃቀም በኅብረተሰቡ የጤና ሁኔታና ሀገራዊ የልማት ተሳትፎ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው” የኢትዮጵያ ጤና መድኅን አገልግሎት
Next article“በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ያስመዘገብነው ታሪካዊ ድል በሌሎችም የግብርና ሥራዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል” ኃይለማርያም ከፍያለው (ዶ.ር)