
ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንቷ ይህን ያሉት በኪጋሊ፣ ሩዋንዳ እየተካሄደ ባለው ‘Women Deliver 2023’ ኮንፍረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
ሴቶች በፖለቲካው ዓለም እየተሳተፉ ቢገኙም፤ ከዚህ የላቀ ትርጉም ያለው ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
አንዲት ሴት ትልቅ ቦታ ስትይዝ ሌሎች ሴቶችን በመደገፍና በማበረታታት አርአያ ልትሆን ይገባልም ብለዋል።
‘Women Deliver’ ኮንፍረንስ በ2007 የተጀመረ ሲሆን፤ ስለ ሴቶች መብት የሚመከርበት በዓለም ትልቁ መድረክ ነው።
ኮንፍረንሱ ከዚህ ቀደም በለንደን፣ ቫንኩቨር፣ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ኳላላምፑር እና ኮፐን ሀገን የተካሄደ ሲሆን፤ በ2023 ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ (ኪጋሊ፣ ሩዋንዳ) ተካሂዷል።
በ2019 በቫንኩቨር፣ ካናዳ በተካሄደው ኮንፍረንስ ላይ ኘሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ መሳተፋቸው ይታወሳል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።
የዘንድሮው የኮንፍረንሱ አዘጋጅ ሀገር ሩዋንዳ የፆታ እኩልነትን ያስከበረች ሀገር በሚል ከዓለም በ6ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን መረጃዎች ያሳያሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!