
አዲስ አበባ: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በችግኝ ተከላ የተሳተፉ አረጋውያን የችግኝን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ገልጸው ወጣቱ ትውልድም ችግኝ በመትከል ኢትዮጵያን አረንጓዴ እንዲያለብሱ ጥሪ አቅርበዋል።
በዛሬው ዕለት ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ መልእክት በአንድ ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መረሐ ግብር በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሲከናወን ውሏል።
በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎችም አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም ከአረጋውያን ጋር አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።
በችግኝ ተከላ መረሐ ግብሩ ሲሳተፋ ያገኘናቸው አረጋውያን አረንጓዴ አሻራቸውን ማስቀመጥ በመቻለቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ችግኞቹ እንዲፀድቁም ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።
በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የፍራፍሬ ችግኞች እና የጥላ ዛፍ ችግኞች ሲተከሉ ውለዋል።
በበለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
