የአማራ ክልል ዕቅዱን ሊያሳካ ከ16 ሚሊዮን ችግኞች በታች ቀርተውታል።

60

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል በአንድ ጀምበር ለመትከል ከያዘው 260 ሚሊዮን ችግኞች መካከል እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ 244 ሚሊዮን 260 ሺህ የሚሆነው ተተክሏል፡፡

የክልሉ ሕዝብ በሁሉም አካባቢ ከማለዳው ጀምሮ ኢትዮጵያን ችግኝ እያለበሰ ነው፡፡

በአማራ ክልል ጀምበር ዘልቃ እስክ ትጠልቅ ድረስ 260 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ ተይዞ ነበር፡፡ በክልሉ ጀምበር ከመጥለቋ ከሰዓታት በፊት የዕቅዱ አብዛኛው ተሳክቷል፡፡

እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ ዕቅዱ እንደሚሳካ ይጠበቃል፡፡

የግብርና ቢሮ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በችግኝ ተከላው 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአረንጓዴ አሻራን መርሐ ግብርን የሕልውና ጉዳይ አድርገን ማየት አለብን” ርእሰ መሥተዳደር ሙስጠፌ ሙሐመድ
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአረጋዊያን ጋር በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጡ።