ዳግማዌ አጼ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 50 ዓመት የምሥረታ በዓልን መነሻ በማድረግ የገቢ ማሰባሰቢያ ውይይት በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡

387

ዳግማዌ አጼ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 50 ዓመት የምሥረታ በዓልን መነሻ በማድረግ የገቢ ማሰባሰቢያ ውይይት በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡

የደብረ ታቦር ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 50ኛ ዓመት ምሥረታ በዓልን መነሻ በማድረግ ነው የገቢ ማሰባሰብ ውይይት እየተደረገ የሚገኘው፡፡

የደብረ ታቦር ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 50ኛ ዓመት አከባበር የጎንደር እና አካባቢው አስተባባሪ ዶክተር ምሕረቴ ኮከብ እንደገለጹት የዓፄ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምሥረታ 50 ዓመት ምሥረታ ከጥር 9-11 ቀናት 2012ዓ.ም በደብረ ታቦር ይከበራል፡፡ በዓሉን መሠረት በማድረግ ለትምህርት ቤቱ ተጨማሪ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ በጎንደር እየተካሄደ ነው፡፡

ገቢው ባለሁለት ፎቅ መማሪያ ክፍሎች ለመገንባት እንደሚውል ዶክተር ምሕረቴ ለአብመድ ተናረዋል፡፡ ግንባታው 6 ሚሊዮን ብር ይጨርሳል ተብሎ የሚገመት ሲሆን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ከሚኖሩ በጎ ፈቃደኞች ለመሰብሰብ መታቀዱን አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡ ዶክተር ምሕረቴ እንደገለጹት አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በጎንደር እና አካባቢው ከሚገኙ ድጋፍ አድራጊዎች ለማሰባሰብ ታቅዷል፡፡ ዛሬ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ባለው ውይይትም የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር፣ አጋር ድርጅቶች እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ 4 ሺህ 500 የሚጠጉ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ ዶክተር ምሕረቴ ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሰራ

Previous articleበኢትዮጵያ የሕዋ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ታሪካዊ ዳራ፡፡
Next articleበደሴ ከተማ የሚገኙ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት በእምነት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዙ፡፡