
ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 500 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር የመተክል መርሐ ግብር በሶማሊ ክልል እየተከናወነ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ባስተላለፉት መልእክት የአረንጓዴ አሻራ ከማንም በላይ ለሶማሊ ክልል እና ለቆላማ አካባቢዎች አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም አርብቶ አደሩ በሚኖርባቸው አካባቢዎች የአረንጓዴ አሻራዎች ያስፈልጋሉ ነው ያሉት፡፡
ደን በተከልን ቁጥር ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ለመከላከል ያስችላልም ብለዋል፡፡
በተደጋጋሚ የሚከተሰውን ድርቅ ለመከላከል ችግኝ መትከል ወሳኝ ጉዳይ መኾኑን አመላክተዋል፡፡ የሕዝቡ ተሳትፎና ግንዛቤ ከፍ እያለ መምጣቱንም ገልጸዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ በአንድ ቀን ብቻ ሳይኾን ተከታታይነት ባላቸው ጊዜያት ሊካሄዱ ይገባል ነው ያሉት፡፡
የተተከሉ ችግኞችን ለመከታተል የሚያስችል ሥራ መሠራቱንም ገልጸዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ ሕይወታችን የሚለውጥ ነው፣ ለሚቀጥለው ትውልድ ወሳኝ የኾነ ሥራ ነው ብለዋል፡፡
ይህን ለእኛ የሕልውና ጉዳይ አድርገን ማየት አለብን ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሁሉም መሳተፍ እንደሚገባውም ርእሰ መሥተዳድሩ መልክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
