
ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ በዚህ አረንጓዴ አሻራ እየተሳተፉ የሚገኙ ዜጎች ሁሉ ለትውልድ የሚተርፍ ሥራ እየሠሩ ነው።
በዚህም እስከ 8:30 ባለው ጊዜ የተተከሉ ችግኞች ብዛት 372 ሚሊየን ደርሷል ብለዋል።
በከተሞች አካባቢ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በነጻ ትራንስፖርት በማቅረብ ጭምር ችግኝ ተከላውን እያቀላጠፉ ይገኛሉ ነው ያሉት።
በአንዷለም መናን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
