
ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የቱርኩ ቲ.አር.ቲ-አፍሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ከፍተኛ የችግኝ መትከል ዘመቻ ማካሄድ መጀመራቸውን በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል።
ኢትዮጵያ በቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር ላይ እያካሄደ እንዳለ ይህም በቀን ውስጥ በርካታ ችግኞችን በመትከል የዓለምን ሪከርድ የሚሰብር መሆኑን ነው የሚዲያው አውታሩ የዘገበው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዲሁም ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው መርሐ-ግብሩን ዛሬ ማለዳ የአፕል ችግኝ በመትከል እንዳስጀመሩትም ቲ.አር.ቲ አስነብቧል።
የቻይናው ሲጂቲኤን-አፍሪካ በበኩሉ፣ 500 ሚሊዮን ችግኞችን በ12 ሰዓታት ውስጥ ለመትከል የሚያስችል ታላቅ መርሐ-ግብር መጀመሩን ገልጾ፣ ይህ ከተሳካ፣ የምሥራቅ አፍሪካን የደን ሽፋን ለማሻሻል ለታቀደው ዕቅድ ትልቅ ብሔራዊ አሻራ ይሆናል ሲል ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
