ከ19 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተከለ መኾኑን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ገለጸ።

42

እንጅባራ: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት በሚካሄደው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ19 ሚሊዮን በላይ የደን፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን እየተከሉ መኾኑን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ አስታውቋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ታደሰ አስፋው (ዶ.ር) እንደገለጹት፦

– በአንድ ጀንበር ከሚተከሉ 29 ነጥብ 9 ሚሊዮን ችግኞች ውስጥ ከ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ የሚኾኑት የፍራፍሬ ችግኞች ናቸው።

– ከ2 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትም ለተከላ ተለይቷል።

– ከ19 ሚሊዮን በላይ የችግኝ ጉድጓድ ተዘጋጅቷል።

– ለችግኝ ተከላዉ ከ400 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ኾነዋል።

– በብሔረሰብ አሥተዳደሩ በ2014 ዓ.ም ከተተከሉ 75 ነጥብ 6 ሚሊዮን ችግኞች ውስጥ 79 ነጥብ 6 በመቶ የሚኾኑት ጸድቀዋል።

አሚኮ በተገኘበት ፋግታ ለኮማ ወረዳ በተረያ ተራራ ላይ በነበረው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግበር ተሳታፊዎች አሻራቸውን ማኖር በመቻላቸው ደስተኞች መኾናቸውን ተናግረዋል።
ተሳታፊዎቹ ለችግኝ ተከላ የተሰጠው ትኩረት በችግኞች እንክብካቤም መደገም እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በተያዘው የክረምት ወቅት በጠቅላላው ከ83 ሚሊዮን በላይ የደንና ፍራፍሬ ችግኝ ለመትከል መታቀዱን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ መረጃ ያመለክታል።

ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የኢትዮጵያን ልማት እንደግፋለን” ኤርትራዊያን ስደተኞች
Next article“የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ማጽደቅና ለውጤት ማብቃት ይገባል” አምባሳደር ሐሰን አብዱልቃድር