“የኢትዮጵያን ልማት እንደግፋለን” ኤርትራዊያን ስደተኞች

38

ደባርቅ: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ዓለምዋጭ የስደተኞች ሳይት የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

በችግኝ ተከላው ኤርትራዊያን ስደተኞች፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት፣ፕላን ኢንተርሽናል እና ሌሎች በስደተኞች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ የተለያዩ ድርጅቶች ኀላፊዎች እና ሠራተኞች፣የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣የአካባቢው ማኅበረሰብ፣የከተማና የወረዳ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል።

የዓለምዋጭ ስደተኞች ሳይት የኮሙዩኒኬሽን ተወካይ አሥተባባሪ አቶ ዳግማዊ ምኒልክ ኤርትራዊያን ስደተኞችና በሳይቱ የሚሠሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የኢትዮጵያን ልማት ደግፈው በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር አሻራቸውን ማስቀመጣቸውን ተናግረዋል።

በተከላው ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈው ከ12 ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸውን አቶ ዳግማዊ ገልጸዋል። መረጃው የዳባት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 80 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል ላይ መኾኑን የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ገለጸ፡፡
Next articleከ19 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተከለ መኾኑን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ገለጸ።