ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ እየገጠመን ያለውን ችግር ለመቀነስ በአረንጓዴ አሻራ ላይ የጀመርነውን ስራ እናጠናክራለን -አቶ ሽመልስ አብዲሳ

51

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሚያ ክልል ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ እየገጠመ ያለውን ችግር ለመቀነስ በአረንጓዴ አሻራ ላይ የተጀመረው ስራ እንደሚጠናከር የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ከምስራቅ ሸዋና ከአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በመሆን በአዳማ አካባቢ ችግኝ ተክለዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባለፉት ዓመታት የኦሮሚያ ክልል ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ብዙ ችግሮችን አስተናግዷል ብለዋል።

በተለይም በክልሉ ቆላማ አካባቢዎች አጋጥሞ በነበረው ድርቅ በሰውና በእንሰሳት ላይ ብዙ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመቋቋም የክልሉ ሕዝብ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የጀመረው ተሳትፎ ውጤት እያስገኘ መሆኑንም ገልጸዋል።

ለአስካሁኑ ስራ የክልሉን ህዝብ ያመሰገኑት አቶ ሽመልስ ችግኝ መትከል የኦሮሞ ሕዝብ ባህል ውስጥ ሰፊ ቦታ ያለው በመሆኑ ሕዝቡ ይህንኑ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም የክልሉ ህዝብ እስከ ማታ ድረስ አሻራውን እንዲያኖር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አሁን የተገኘውን ሰላም በማጽናት የበለጠ የልማት ሥራ እንደሚሠራ አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።
Next articleበአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 80 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል ላይ መኾኑን የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ገለጸ፡፡