
ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በትግራይ ክልል በአንድ ቀን 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር ላይ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በተገኙበት ነው እየተካሄደ ያለው።
አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ባደረጉት ንግግር አሁን የተገኘውን ሰላም በማጽናት የበለጠ የልማት ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ሰላሙን ለማጽናት የፌዴራል መንግሥት ጠንክሮ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የክልሉ ጊኤአዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው፤ ሰላም ሰፍኖ ወደዚህ አይነት ተግባር መመለስ መቻሉ መልካም መሆኑን በመጥቀስ፤ የተገኘውን ሰላም ለማጽናት ጠንክረው እንደሚሰሩ አብራርተዋል።
በመላው አገሪቱ ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ እስከ 5:30 ባለው ሰዓት 247 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት መግለጹ ይታወሳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
