“ችግኞችን ከመትከል ባለፈ እንዲጸድቁ ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግ ይገባል” የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ

42

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ‹‹ነገን ዛሬ እንትከል›› በሚል መልዕክት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እንዳሉት በሰው ልጆች የጥንቃቄ ጉድለት በሚፈጠር የአየር ንብረት ለውጥ በሥነ ምሕዳር እና በሰው ልጆች ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ፈተና ኾኗል፡፡ ችግሩን ለመፍታት ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተገበረች ትገኛለች፡፡ በአረንጓዴ ልማቱም ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አንስተዋል፡፡

አቶ አደም እንዳሉት ችግኝ ሲተከል የባለሙያዎችን ምክረ ሐሳብ በተከተለ መንገድ ሊኾን ይገባል፤ የተተከሉትንም እንዲጸድቁ ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ አኹን ላይ እየተከናወነ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ለቀጣዩ ትውልድ ተነሳሽነትን ለመፍጠር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል፡፡

የተሠሩ ሥራዎችን ለሌሎች ሀገራት በማስተዋወቅ በጎ ተጽዕኖ ለመፍጠር ትልቅ አቅም እንዳለውም ገልጸዋል፡፡ በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራትም በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመግታት ተሞክሮውን በመውሰድ እንዲሠሩ እድል የሚሰጥ እንደኾነ ነው ያነሱት፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleችግኝ ከመትከል ባለፈ የተከለሉ ደኖችን በመጠበቅ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እየሠራ መኾኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
Next article“የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ግብን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል” የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር