
በሞጣ ካጋጠመው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፤ ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መለሷም እየተነገረ ነው፡፡
ከዛሬ ማለዳው ጀምሮ መደበኛ የከተማዋ እንቅስቃሴ ቀጥሏል፡፡ አንዳንድ የንግድ ተቋማት ሥራ ጀምረዋል፡፡ ከተማዋ ከባሕር ዳር – አዲስ አበባ የሚያልፈው ዋና መስመር ላይ እንደመሆኗ ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች ከሌሊት ጀምሮ ነበር መደበኛ እንቅስቃሴ የተጀመሩት፡፡ ዞር ዞር ብለን በተመለከትናቸው ቤተ እምነቶች አካባቢ ግን የነበረው ችግር ድባብ ሙሉ በሙሉ የተቀረፈ አይመስልም፡፡
ከምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ ተስፋዬ ባገኘነው መረጃ መሠረት እስካሁን 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ አካባቢውን ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲመለስ የማድረጉ እና ተጠርጣሪዎችን እየለዩ በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሥራም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ዘጋቢ፡- የማነብርሃን ጌታቸው -ከሞጣ
