“በአንድ ጀንበር ዳግም ታሪክ እንሥራ” ርእሰ መሥተዳድር አወል አርባ

27

ባሕር ዳር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 500 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር የመትከል መርሐ ግብር በአፋር ክልል እየተካሄደ ነው፡፡
\
በመርሐ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳደር አወል አርባ የአረንጓዴ አሻራ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያመጣ ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመቋቋም ትልቅ ሚና ያለው መኾኑን ገልጸዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ በኢትዮጵያ በደን መመናመን ምክንያት እየተከሰተ ያለውን አካባቢያዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመከላከል ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል፡፡
በተለይም በአርብቶ አደሩ የሚከሰተውን ድርቅ እንደሚከላከልም ገልጸዋል፡፡

በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ተግባር መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በትብብር፣ በአንድነት ካለመበት መድረስ እንደሚቻል ለዓለም የምናሳይበት ነው ብለዋል፡፡
ከፍተኛ ተግዳሮት ለኾነው የአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያ የራሷን ድርሻ እየተወጣች መኾኗን ማሳያ እንደኾነም አስገንዝበዋል፡፡

የዛሬ ችግኞች የነገ ምግብ፣ ጥላና ውበት መኾናቸውን ተገንዝበን የተከልናቸው ችግኞች እንዲጸድቁ ሁሉም የበኩሉን ሀገራዊ ግዴታ እንዲወጣም አሰገነዝባለሁ ነው ያሉት፡፡
የታሪኩ አካል ለኾናችሁ ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ፣ በአንድ ጀንበር ዳግም ታሪክ እንሥራ ብለዋል ርዕሰ መሥተዳድሩ፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለልጆቻችን አረንጓዴ ሸማ የለበሰች ኢትዮጵያን እናቆያቸው” የሰሜን ምዕራብ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ብርሃኑ በቀለ
Next articleበሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 5:30 ድረስ 247 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል።