”የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ በተጨማሪ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለከተማዋ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ነው“ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሀይ

43

ጎንደር: ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ሥራው በተጨማሪ ባለፉት አምስት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ አሻራውን እያሳረፈ ነው።

ባለፉት ሁለት ዓመትና የዘንደሮውን ጨምሮ ከ300 ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን ተናግረዋል። ችግኞችን ከመትከል ባለፈ እንዲጸድቁ ከፍተኛ ጥበቃ እንደሚደረግም ዶክተር አስራት ገልጸዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሀይ እንደ ከተማ አሥተዳደር ከ233 ሺህ በላይ ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል ሥራ እየተከናወነ መኾኑን ገልጸዋል። ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ በተጨማሪ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለከተማዋ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ነው ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የዩኒቨርሲቲውን ሠራተኞች በማስተባበር ከ10 ሺህ በላይ ችግኞች ይተከላሉ ተብሏል።

ዘጋቢ ፡- ደስታ ካሳ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleችግኝ መትከል የመልካም ትውልድ መገለጫ መሆኑን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
Next article“ለልጆቻችን አረንጓዴ ሸማ የለበሰች ኢትዮጵያን እናቆያቸው” የሰሜን ምዕራብ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ብርሃኑ በቀለ